1.የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት አብድ ኢሌ ቀኝ እጅ የነበሩና ላለፉት አስርተ አመታት በክልሉ ለተፈፀሙት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ፣ የመልካም አስተዳደር ዕጦት፣የተንሰራፋፈ ሙስና፣ግድያና አፈና ወዘተ… በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አስፈፃሚ አልፎ ተርፎም ፈፃሚ የነበሩ አካላት ናቸው። 

ፕሬዚዳንት ሙስጠፈ ክልሉን መምራት ከጀመሩ ሰባት ወር ገደማ ሆናቹዋል።
በዚህ አጭር ጊዜ በርካታ የተሰሩ አመርቂ ውጤቶች እንዳሉ ሁሉ ፣ በብዙ ምከንያቶች የተፈለገውን ውጤት ያላስመዘገቡ ስራዎችም አሉ። የሆነ ሆኖ የአስተዳደሩ ዋነኞቹ ማነቆዎች የሚከተሉት ናቸው ።

ሆኖም እነዚህ አካላት ሕዝባቸውን ይቅርታ መጠየቅ ና መካስ ስገባቸው፣ እነሱ ግን በተቃራኒው በክልሉ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር እና ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት ያሴራሉ።በሙስና ከደሃው ሕዝብ የዘረፉትን ስፊር ቁጥር የሌለውን ገንዘብ ለዚሁ እኩይ ለሆነዉ ተግባራቸው ማስፈፀሚያ ያውላሉ። የዋሁን ሕዝቡን እርስ በርሱ በማባላት ለተራ ፖለቲካ ፍጆታ ለመጠቀም ይሞክራሉ ።

የሚገርመው ደግሞ ላለፉት አመታት በሰሯቸው ስራዎች ማፈር ስገባቸው፣ አይናቸውን በጨው አጥበው ራሳቸውን መላዕክት አድርገው በመቁጠር፣ ለሕዝቡ አጉል ተቆርቋሪ መስለው መቅረባቸው ነው። ታድያ ምነው ትላንት በሕዝቡ ላይ ያ ሁሉ መከራ ና ስቃይ ሲወርድበት ድምጻችሁ ጠፋሳ¡?
የካቢኔው አባላት ስለነበራችሁ መቼም አልሰማንም አትሉም አይደል?? ለስሙ “የሌባ አይነ ደረቀ መልሶ ልብ አድሪቅ” እንደሚባለው ሁሉ… አልሰማንም ብትሉም አይደንቀኝም ።
———————————-

2.ሁለተኞቹ ደግሞ በተለያዩ አገራት በስደት ይኖሩ የነበሩ ና ለውጡን ተከትለው ወደ እናት አገራቸው የገቡ የክልሉ ተወላጅ ድያስፖራዎች ናቸው።
እነዚህ አካላት የተፈጠረው አጋጣሚ በመጠቀም፣ ባዕድ አገር ላባቸውን ጥፈ አድርገው ያካበቱትን ገንዘብ ወደ አገራቸወ ኢንቨስት ማድረግና፣ በልማት ረገድ የበኩላቸውን መወጣት ነበረባቸው ።

እነሱ ግን ወደ አገራቸው የተመለሱት በክልሉ የሚሰጡትን የመንግስት የልማት ኮንትራቶችን በሞኖፖሊ ለመቆጣጠር ፣ስልጣን ለማግኘት ና የክልሉን ሀብት ለመቀራመት ይመስላል ።ይህም ተግባራቸው አልሳካ ስላቸው ፣ የተለያዬ ፕሮፖጋንዳዎችን በመንዛት ሕዝቡ በአስተዳደሩ ላይ ያለውን እምነት ለመሸሸርና እንድሁም ሕዝብን ከሕዝብ በሚያጋጩ ድርጊቶች ተጠምዷል ።

እነዚህ አካላት የቀድሞ የክልሉ አስተዳደር ይፈፀም የነበረው የሰብዓዊ መብት ረገጣ በመቃወም በተለያዩ የአለም ሀገራት በተለያየ መልኩ ስቃወሙ የነበሩና ታሪክ የሚያውሰው ስራ በመሠራት የሕዝብ አለኝታ መሆናቸው አስመስክሯል ። ይህንን አኩሪ ስራቸው ወደ ጎን ብለው በተራ የጥልፈልፈና ሴራ ፖለቲካ ውስጥ ስናገኛቸው አሳዝኖናል።ውድ ዲያስፖራዎች የታገላችሁት ለሕዝቡ ነፃነት እና እኩል ተጠቃሚነት ከሆነ ፣ ያንን ጀብድ ስራችሁ በማስታወስ ወደ ቀልባችሁ ተመለሱ ና ከሕዝቡ ጋር የትግላችሁን ፍሬ አጣጥሙ።

ማሳሰቢያ 
ለውጡን ተከትሎ የተገኝዉ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት (ፌሬደም ኦፍ ኢሥፒች) በመጠቀም የአስተዳደሩን ክፍተት በመፈለግ የሚተቹትን ወይም የሚነቀፋትን አካላት እናበረታታለን፣ለዲሞክራሲያችን ዕድገትም አዎንታዊ አስተዋጵኦ ያደርጋል። ነገር ግን ይህን መብታቸው አላግባብ በሆነ መልኩ በመጠቀም ህዘብን ከ ህዝብ ለማጋጨት ወይም ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ማንኛውም አካላት በሕግ ልጠየቁ ይገባል እንላለን ።

SR News