ላለፉት አመታት የሶማሌ ክልልን ፖለቲካ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመዘወር ክልሉን በሞግዚትነት ስታስተዳድሩ ከርማችኋል። በነዚያ አስከፊ አመታት በሶማሌ ሕዝብ ያደረሳችሁት በደል፣ ስቃይ፣አፈና ፣ ግድያ ወዘተ..የማይረሳና በታሪክ መዝገብ የሚቀመጥ ይሆናል።

በክልሉ ታህዱት የነበረው ከፍተኛ የኮንትሮባንድ ንግድ ስለተቋረጠባችሁ እረፍት አሳቷቹዋል። በሶማሌና ኦሮሞ ሕዝቦች መካከል ጦሪነት ለመፍጠር የጠነሰሳችሁት ሴራም ተነቅቶባቿል ። አሁን ደግሞ በአፈር ና በሶማሌ ክልል መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት እንደ ጥሩ አጋጣሚ አድርጎ በመጠቀም ፤ በአፈር በኩል ሰርጎ ለመግባትና ፣ በክልሎቹ መካከል ጦሪነት እንድነሳ ሴራዎችን እያሴራችሁ ነው።ነገር ግን አይሳካላችሁም።

የአፈርና የሶማሌ ሕዝብ ወንድማማቾች ሕዝቦች ናቸው። ማንም ልለያያቸው አይችልም ። በመካከላቸው ያለውን አለመግባባት ፣ ያለማንም ጣልቃ ገብነት በሰለጠነ መልኩ መፍታት የሚችሉ ህዝቦች ናቸው።

ለማስታወስ ያክል የሶማሌ ክልል አቋምም እነዚህን አለመግባባቶች ሕገ-መንግስታዊ በሆነ መልኩ መፍታት አለባቸው ነው።

SR News